News

ጳጉሜ 1 – የእምርታ ቀን (የምግብ ሉዓላዊነትና ምርታማነት) ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ተያይዞ የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋጡ ተግባራት የሚከናወኑበት ዕለት ነው። በየአካባቢው ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የተደረገውን ሽግግር የሚያሳዩ የሰብል ማሳዎች ጉብኝት ይደረጋል ብለዋል።

ጳጉሜ 2 – የማንሰራራት ቀን (ልማትና ኢኒሼቲቮች) በተለያዩ አከባቢዎች የተሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች የሚጎበኙበት እና የፓርቲ ኢኒሼቲቭ ተግባራት አፈጻጸም የሚገመገምበት ቀን እንደሆነም ተገልጿል።

ጳጉሜ 3 – የፅናት ቀን (የፀጥታ ሀይላት ክብርና አገር ፍቅር) የፀጥታ ሀይሎችን የሚደግፍና የሚያጀግን ቀን ነው። በከተሞች መስመሮች የሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ፣ በአደባባይ በመሰለፍ ብሔራዊ መዝሙር መዘመር እና ባንዲራ የመስቀል ስነ-ሰርዓት ይከናወናል ብለዋል።

ጳጉሜ 4 – የህብር ቀን (አብሮነትና ሰው ተኮር ስራዎች) አብሮነትን፣ መረዳዳትን እና ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ስራዎች ይከናወናሉ። በተለይም ለችግረኞች እና ለድሃ ድሃዎች ድጋፍ የሚደረግበት ሰው ተኮር ስራዎች የሚሰሩበት እንደሆነ ገልፀዋል።

ጳጉሜ 5 – የነገ ቀን (ዲጂታል ትውልድና የወደፊት እይታ) ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ ተግባራት የሚከናወኑበት ነው። ወጣቶች በ«ኢትዮ ኮደርስ» (Ethio Coders) መርሃ ግብር ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይደረጋል፤ እንዲሁም የ«ሞሰብ አንድ ማዕከል» ግንባታ የጀመሩ አካላት ጉብኝት ይካሄዳል ብለዋል።

‎የእንቁጣጣሽ በዓል (የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት) በየዓመቱ መስከረም 1 ቀን የሚከበር ሲሆን፣ «እንቁጣጣሽ» የሚለው ቃል ትርጉም እና የበዓሉ አከባበር አመጣጥ ከታሪክ፣ ከሃይማኖትና ከተፈጥሮ መታደስ ጋር የተያያዙ ጥልቅ ምስጢሮች አሉት

የቃሉ ዋና ዋና ትርጉሞችና የበዓሉ አከባበር ታሪክ እንደሚከተለው ይጠቃለላል፦1. የ«እንቁጣጣሽ» ቃል ትርጉምና አመጣጥ«እንቁ ለጣትሽ ነው» ወይም «እንቁ ለአምላክሽ»፦ ትውፊቱ እንደሚነግረን፣ የሳባ ንግሥት (ንግሥት ማክዳ) የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛ ከተመለሰች በኋላ፣ የሀገሪቱ መኳንንትና ሕዝብ ለንግሥቲቱ ክብር ሲሉ «እንቁ ለአምላክሽ/ለጣትሽ ነው» በማለት በከበሩ ዕንቁዎችና በስጦታ ተቀበሏት።

ይህ ኃይለ-ቃል በጊዜ ሂደት እየተለወጠ «እንቁጣጣሽ» የሚል ስም እንደያዘ ይታመናል።«ዕንቁ ዕጣ ወጣሽ»፦ ሌላው ትርጉም ደግሞ ክረምቱ አልፎ፣ ምድር በዓይነ ማራኪ አበቦች አጊጣ፣ አዲሱ ዘመን ሲመጣ «የዕንቁና የደስታ ዕጣ ደረሰሽ/ወጣልሽ» የሚለውን መልካም ምኞት ይገልጻል።

‎2. የበዓሉ ዋና ዋና የአከባበር ሥርዓቶች በዓሉ የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያውያን አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን በይቅርታና በተስፋ የሚቀበሉበት ማኅበራዊ ትስስር ነው፦የልጃገረዶች «አበባዮሽ» ጨዋታ፦ ልጃገረዶችና ወጣቶች አገር በቀሉን ቢጫ «የመስቀል ወፍ» ወይም «አደይ አበባ» በመያዝ፣ በባህላዊ አልባሳት አጊጠው በየቤቱ በመዘዋወር «አበባዮሽ» ይዘፍናሉ። ለቤቱ ነዋሪዎችም መልካም አዲስ ዓመት እየተመኙ የሳሏቸውን ስዕሎች በስጦታ ያበረክታሉ።

‎የቤቱ ባለቤቶችም ምላሽ በመስጠት ለልጆቹ ሳንቲም ወይም ዳቦ ይሰጣሉ። የወጣቶች «እንቁጣጣሽ / ሺህ አመት» ጨዋታ፦ ወንዶች ልጆችም በተራቸው ጅራፍ በማጮህ፣ ችቦ በማብራት እና ባህላዊ ዘፈኖችን በመጫወት አዲሱን ዓመት በደስታ ይቀበላሉ።

‎የቤተሰብ ስብስብና ባህላዊ ምግቦች፦ በዕለቱ ማለዳ ላይ የቤተሰብ አባላት አዲስ ልብስ ለብሰው አብረው ይጸልያሉ። በመቀጠልም እንደ ዶሮ ወጥ፣ የዓመት በግ ታርዶ ምሳ በጋራ ይበላል።

‎በዓሉ ያለ ቡና ሥርዓትና ያለ ባህላዊው ዳቦ (ኅብስት) አይታሰብም።በአጠቃላይ፣ እንቁጣጣሽ ማለት ጨለማውና ዝናባማው የክረምት ወራት አልፎ፣ ምድር በአደይ አበባ አጊጣ፣ ብርሃን የሚፈነጥቅበትና አዲስ ተስፋ የሚሰበክበት የኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ በዓል ማለት ነው

‎በጥቅቱ የበአሉን ትርጉምና አከባበር ይህን ካልን በአሉ የሰላም የፍቅር የአንድነትና የመከባበር እንዲሁ የተቸገሩትን በረዳት የምናከብረበት በአል ይሁን በድጋሚ እንኳን ለ2019 የእንቁጣጣሽ በአል በሰላም አደረሳችሁ !!!!!!

\‎በዚህ ፕሮግራም ላይ የሁሉም ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት እና የከንቲባ ፅ/ቤት ኃላፊዎች የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ባለሙያዎች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎች የአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎች አንዲሁም የህዝብ ቅሬታና አስተዳደራዊ ፍትህ ዘርፍ ባለሙያዎች ተሳትፈዋ

‎የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ ይህ መድረክ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች በማስቀጠል ያሉትን ችግሮች በመፍታት በቀጣይ ተግባሮችን በትስስር ና በመቀናጀት ለመስራት ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ነው በማለት መድረኩን በይፍ መከፈቱን አብስረዋል።

‎የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምን በዞኑ አስተዳደር ፅ/ ቤት የዕቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ባለሙያ አቶ ደረጄ ጌታነህ የቀረበ ሲሆን ፦

‎ተቋሙ ባቀዳቸው ዋና ዋና ግብና ዝርዝር ተግባራት ላይ የተከናወኑ ተግባራት በክንውን ወቅት የታዩ እና ያልተሻገርናቸው መሰረታዊ ችግሮች በአፈፃፀም ረገድ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች የተመዘገቡ ምርጥ ተሞክሮዎች በዝርዝር ቀርበዋል በተለይ ተቋሙ ከተቋቋመበት ደንብ አንፃር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ በዘርፈ ብዙ ተግባራት አፈፃፀም፣ በአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ አፈታት እንዲሁም የህዝብ ቅሬታና አስተዳደራዊ ፍትህ ዘርፍ ላይ ከደንቡ አንፃር የተከናወኑ በአጠቃላይ የተቋሙን ፒላር መነሻ በማድረግ የተከናወኑ በምርጥ ተሞክሮነት የሚወሰዱ ጉዳዩችን የዳሰሰ ሪፖርት ቀርቧል።

‎ በሌላ መንገድ በ2019 ዓ.ም የታቀዱና ከዞን እስከ ወረዳ መፈፀም ያለባቸውን ዋና ዋና ግብና ተግባራት ዙሪያ በባለሙያው የዕቅድ ትውውቅ ተደርጓል።

‎ በተጨማሪም የታቀዱ ግቦችና ተግባራትን የበለጠ በማሳለጥ የተሻለ የአፈፃፀም ውጤት ለማስመዝገብ ይቻል ዘንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ በ2019 በጀት ዓመት ሊያከውናቸው የተያዙ ተግባራትን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪው በአቶ ደመላሽ በላይ የቀረበ ሲሆን ።

‎የምስራቅ አማራ ፕላን ኢንስቲቲዩት በከተሞች ታዳጊ ከተሞች የፕላን አተገባበር ዙሪያ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የወጣውን ደንብ አስመልክቶ የግንዛቤ ፈጠራ በተቋሙ ተወካይ ኃላፊ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን።

‎ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የዕውቅና ፕሮግራም ተከናውኗል በዚህም መሰረት ከወረዳዎች

Scroll to Top