በዚህ ፕሮግራም ላይ የሁሉም ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት እና የከንቲባ ፅ/ቤት ኃላፊዎች የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ባለሙያዎች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎች የአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎች አንዲሁም የህዝብ ቅሬታና አስተዳደራዊ ፍትህ ዘርፍ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ ይህ መድረክ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች በማስቀጠል ያሉትን ችግሮች በመፍታት በቀጣይ ተግባሮችን በትስስር ና በመቀናጀት ለመስራት ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ነው በማለት መድረኩን በይፍ መከፈቱን አብስረዋል።
የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምን በዞኑ አስተዳደር ፅ/ ቤት የዕቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ባለሙያ አቶ ደረጄ ጌታነህ የቀረበ ሲሆን ፦
ተቋሙ ባቀዳቸው ዋና ዋና ግብና ዝርዝር ተግባራት ላይ የተከናወኑ ተግባራት በክንውን ወቅት የታዩ እና ያልተሻገርናቸው መሰረታዊ ችግሮች በአፈፃፀም ረገድ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች የተመዘገቡ ምርጥ ተሞክሮዎች በዝርዝር ቀርበዋል በተለይ ተቋሙ ከተቋቋመበት ደንብ አንፃር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ በዘርፈ ብዙ ተግባራት አፈፃፀም፣ በአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ አፈታት እንዲሁም የህዝብ ቅሬታና አስተዳደራዊ ፍትህ ዘርፍ ላይ ከደንቡ አንፃር የተከናወኑ በአጠቃላይ የተቋሙን ፒላር መነሻ በማድረግ የተከናወኑ በምርጥ ተሞክሮነት የሚወሰዱ ጉዳዩችን የዳሰሰ ሪፖርት ቀርቧል።
በሌላ መንገድ በ2019 ዓ.ም የታቀዱና ከዞን እስከ ወረዳ መፈፀም ያለባቸውን ዋና ዋና ግብና ተግባራት ዙሪያ በባለሙያው የዕቅድ ትውውቅ ተደርጓል።
በተጨማሪም የታቀዱ ግቦችና ተግባራትን የበለጠ በማሳለጥ የተሻለ የአፈፃፀም ውጤት ለማስመዝገብ ይቻል ዘንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ በ2019 በጀት ዓመት ሊያከውናቸው የተያዙ ተግባራትን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪው በአቶ ደመላሽ በላይ የቀረበ ሲሆን ።
የምስራቅ አማራ ፕላን ኢንስቲቲዩት በከተሞች ታዳጊ ከተሞች የፕላን አተገባበር ዙሪያ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የወጣውን ደንብ አስመልክቶ የግንዛቤ ፈጠራ በተቋሙ ተወካይ ኃላፊ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን።
በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የዕውቅና ፕሮግራም ተከናውኗል በዚህም መሰረት ከወረዳዎች
1ኛ. ምንጃር ሸንኮራ
2ኛ. ሞጃና ወደራ
3ኛ. ሞረትና ጅሩ
4ኛ. ሲየደብርና ዋዩ
5ኛ. መንዝ ጌራ ወረዳዎች የዋንጫና የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
