የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የጳጉሜን ቀናት በሰፊው ዝግጅት ሊያከብር መሆኑን አስታወቀ ።

የሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የዘንድሮውን የጳጉሜን ቀናት በይፋ ለማክበር የሚያስችሉ ሁነቶችን አቅዶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል።

እያንዳንዱ የጳጉሜን ቀን የሚከተሉትን ይዘቶችና የተለዩ መርሃ ግብሮች ይዞ ይከበራል ፦

ጳጉሜ 1 – የእምርታ ቀን (የምግብ ሉዓላዊነትና ምርታማነት) ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ተያይዞ የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋጡ ተግባራት የሚከናወኑበት ዕለት ነው። በየአካባቢው ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የተደረገውን ሽግግር የሚያሳዩ የሰብል ማሳዎች ጉብኝት ይደረጋል ብለዋል።

ጳጉሜ 2 – የማንሰራራት ቀን (ልማትና ኢኒሼቲቮች) በተለያዩ አከባቢዎች የተሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች የሚጎበኙበት እና የፓርቲ ኢኒሼቲቭ ተግባራት አፈጻጸም የሚገመገምበት ቀን እንደሆነም ተገልጿል።

ጳጉሜ 3 – የፅናት ቀን (የፀጥታ ሀይላት ክብርና አገር ፍቅር) የፀጥታ ሀይሎችን የሚደግፍና የሚያጀግን ቀን ነው። በከተሞች መስመሮች የሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ፣ በአደባባይ በመሰለፍ ብሔራዊ መዝሙር መዘመር እና ባንዲራ የመስቀል ስነ-ሰርዓት ይከናወናል ብለዋል።

ጳጉሜ 4 – የህብር ቀን (አብሮነትና ሰው ተኮር ስራዎች) አብሮነትን፣ መረዳዳትን እና ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ስራዎች ይከናወናሉ። በተለይም ለችግረኞች እና ለድሃ ድሃዎች ድጋፍ የሚደረግበት ሰው ተኮር ስራዎች የሚሰሩበት እንደሆነ ገልፀዋል።

ጳጉሜ 5 – የነገ ቀን (ዲጂታል ትውልድና የወደፊት እይታ) ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ ተግባራት የሚከናወኑበት ነው። ወጣቶች በ«ኢትዮ ኮደርስ» (Ethio Coders) መርሃ ግብር ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይደረጋል፤ እንዲሁም የ«ሞሰብ አንድ ማዕከል» ግንባታ የጀመሩ አካላት ጉብኝት ይካሄዳል ብለዋል።

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች እነዚህ አምስቱም የጳጉሜን ቀናት ህዝብን ባሳተፈ መልኩ በልዩ ትኩረት ይተገበራሉ ።

Facebook

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top